Telegram Group Search
የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ምድረ ግቢ የተሰሩት ሥራዎች ጉብኝት በምስል ፡-
የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት መቀላቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አካል ነው – አምባሳደር ምስጋኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት ለመቀላቀል የምታደርገው ጥረት የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ዋና አካል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለፁ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው በዓለም የንግድ ድርጅት የአባልነት ክፍል ዳይሬክተር ከሆኑት ማይካ ኦሽካዋ ጋር ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጀት አባል የምትሆንበት ሂደት እንዲፋጠን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/246106
Live stream finished (40 minutes)
ዳኛ ነኝ ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ከባለጉዳይ ጉቦ የተቀበለው የፍ/ቤት ሰራተኛ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳኛ ነኝ ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ከባለጉዳይ 200 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለው የፍርድ ቤት ሰራተኛ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጥቷል። የግራ ቀኝ ማስረጃን መርምሮ የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው። የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ አዳማ ምድብ ዐቃቤ ሕግ እንድሪስ ዑመር…

https://www.fanabc.com/archives/246122
አቶ አሕመድ ሽዴ ከካናዳ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ጋር በሀገራቱ የኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከካናዳ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር አሕመድ ሁሴን ጋር በሁለቱ ሀገራ የኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡ አቶ አህመድ ሺዴ በወቅቱ፥ የካናዳ መንግስት ለኢትዮጵያ ልማት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ደረጃ የሚያደርገውን የቆየና ተከታታይነት ያለው ድጋፍ አድንቀዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ እየታዩ ያሉ ለውጦችን ከግምት…

https://www.fanabc.com/archives/246127
በብልጽግና ፓርቲ እና ሕወሓት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፖለቲካዊ ውይይት በመቀሌ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ እና በሕወሓት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፖለቲካዊ ውይይት ለሦስተኛ ጊዜ በመቀለ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል::

በውይይቱም÷ ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረዋል፡፡

ከምክክሩ በኋላም የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ነው የተገለጸው፡፡

https://www.fanabc.com/archives/246130
በአማራ ክልል ሰላም እየሰፈነ በመምጣቱ የልማት ሥራዎችን በስፋት ማከናወን መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰላም እየሰፈነ በመምጣቱ የልማት ሥራዎችን በስፋት ማከናወንና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ ማስመረቅ መቻሉን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከፍተኛ አመራሮች መድረክ፣ በጎርጎራ የተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባና የባህር ዳር ከተማ የአዲሱ…

https://www.fanabc.com/archives/246138
የካርቱም ቀጣናዊ ተልዕኮ ማስፈጸም ማዕከል /ሮክ/ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የካርቱም ቀጣናዊ ተልዕኮ ማስፈጸም ማዕከል /ሮክ/ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል። በአፍሪካ ሕብረት ሥር የተቋቋመው ሮክ በአዲስ አበባ የመከረው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣…

https://www.fanabc.com/archives/246143
የሩሲያ የማጥቃት ዘመቻ መበርታቱን ተከትሎ የዩክሬን ወታደሮች ማፈግፈጋቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የማጥቃት ዘመቻ መበርታቱን ተከትሎ ዩክሬን ወታደሮቿን ከካርኪቭ ግዛት ድንበር አካባቢ ከሚገኙ በርካታ መንደሮች እንዲያፈገፍጉ ማድረጓ ተገለጸ፡፡ የዩክሬን ጦር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፤ ወታደሮቹ በከባድ ተኩስ ውስጥ አልፈው ወደ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ይበልጥ ምቹ ወደ ሆኑ ሁለት አካባቢዎች ተዛውረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪም ወታደሮቻቸው አዲሱን ድንበር…

https://www.fanabc.com/archives/246148
ማስታወቂያ!

እንኳን አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡

በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡

ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሰረትም ፦

1. አምባሳደር ፍስሐ ሻውል ገብሬ

2. አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ወልደየስ

3. አምባሳደር ለገሰ ገረመው ሃይሌ

4. አምባሳደር ደሊል ከድር ቡሽራ

5. አቶ እስክንድር ይርጋ አስፋው

6. አቶ ልዑልሰገድ ታደሰ አበበ

7. ወይዘሮ ናርዶስ አያሌው በላይ

8. አቶ ብሩክ መኮንን ደምሴ

9. አቶ ቴዎድሮስ ግርማ አበበ

10. አቶ መኩሪያ ጌታቸው ወርቁ ን በባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት

እንዲሁም፦

1 . አቶ በትረ መንግስቱ ብርሃኑ

2 . አቶ ዮሃንስ ፈንታ ወልደጊዮርጊስ

3. አቶ ኃይለሥላሴ ሱባ ገብሩ

4 . አቶ ንጉስ ከበደ ካሳው

5. አቶ ዘሪሁን አበበ ይግዛው

6. አቶ ተሾመ ሹንዴ ሀሚጦ

7 . አቶ ሌሊሳ ብርሃኑ ገለታ

8 . አቶ ደረጀ በየነ ደምሴ

9 . አቶ ሰብስቤ ባዴ አድባብ

10 . አቶ ነብዩ ተድላ ነጋሽ

11 . አቶ አንተነህ አለሙ ሰንበቴ

12 . ወይዘሪት ለምለም ፍስሃ ምናለ

13 . አቶ አንዋር ሙክታር መሀመድ

14 . አቶ አብርሃም መንግስቱ ገመቹ ን በአምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያና አዘርባጃን የፀጥታና ደኅንነት ዘርፎችን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመረጃ፣ የፀጥታና ደኅንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሀገራቱን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሌሎች ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም ተስማሙ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

በውይይታቸውም የደኅንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ለማጠናከር የሚያስችሉ የቀጣይ ስራዎች ላይ መክረናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በመረጃ፣ የፀጥታና ደኅንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም ተስማምተናል ነው ያሉት።
Live stream finished (1 hour)
2024/05/16 04:18:09
Back to Top
HTML Embed Code: